‹‹ስድስት ሚሊዮን አይሁዶች ከተፈጁ ሰባ ዓመታት በኋላ የኢራን መሪዎች አገሬን ለማውደም ተማምለዋል፡፡

‹‹አሜሪካና ሌሎች የጥላቻ ኃይሎች በያዙት የጥላቻ መንገድና በአሻጥር ከቀጠሉ ሰሜን ኮሪያ በማንኛውም ጊዜ በኑክሌር ኃይል ለመጋፈጥ ዝግጁ ናት፡፡››

‹‹በዓለም ዙሪያ በርካታ ሰዎች የሚበሉት አጥተው ለኳስ ተጫዋች ቢሊዮን ዶላሮችን ማፍሰስ ከማሳቀቁም በላይ፣ የእግር ኳስ ለዛን እያጠፋው ነው፡፡››

‹‹ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ለፊርማ የተዘጋጀው የሰላም ስምምነት ሰነድ ለውጥ ካልተደረገበት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንደሚፈርሙ አረጋግጥላችኋለሁ፡፡››

‹‹ከዚያ ጦርነት አንዳች ግንኙነት የሌላቸውን ልጆቻችንን፣ የልጅ ልጆቻችንንም ሆነ ወደፊት የሚመጣውን ትውልድ ስላለፈው ጊዜ ይቅርታ እንዲጠይቁ ማድረግ አይገባንም፡፡››

‹‹ለተሳትፏችሁ ወሰኑ ሰማይ ነው››

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ የኦሮሚያ ክልል ዳያስፖራ ሳምንት መከበር አስመልክቶ ሐምሌ 27 ቀን  2007 ዓ.ም.

‹‹የጦር ኃይላችንን ወደ ጦር ሜዳ መላክ አያስፈልገንም፤ ኢትዮጵያውያን ብርቱና ጽኑ ተዋጊዎች ናቸውና፡፡››

Pages