ከአክሱም ከተማ በስተሰሜን ምሥራቅ አቅጣጫ 56 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ጥንታዊቷ ይሓ ከተማ ትገኛለች፡፡ መነሻችን ከነበረው አክሱም ወደ ዓድዋና ዓዲግራት የሚወስደውን ዋና ጎዳና ወደ ጎን ትተን 5 ኪሎ ሜትር ከተጓዝን በኋላ ይሓ ደረስን፡፡ ተጠጋግተው የሚታዩት ህድሞ ቤቶች ረዥም ዓመት እንዳስቆጠሩ ከሚገኙበት ሁኔታ መረዳት ይቻላል፡

በኢትዮጵያ ‹‹ከ80 በላይ ብሔር ብሔረሰቦች›› ይኖራሉ እየተባለ በተለይ ከሩብ ምእት ዓመት ወዲህ ከመንግሥት ለውጥ በኋላ ሲነገር ይሰማል፡፡ በአገሪቱ ያሉት ብሔረሰቦች ቁጥር በርግጥ ስንት ነው የሚለውን ለመወሰን በተለይ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሚገኘው የኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ባህሎች አካዴሚና በፌዴሬሽን ምክር ቤት አማካይነት እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑ ከተነገረ ቆይቷል፡፡

የሰማዕቱ አርበኛ ጳጳስ አቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ዳግም ተከላ በጥር መጨረሻ ሲከናወን የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ፣ ለመንግሥትና ለኢትዮጵያውያን ሁሉ ያስተላለፉት ጥብቅ መልዕክት ሌላኛውን በፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ ሰማዕት የሆኑትን ብፁዕ አቡነ ሚካኤልን መታሰቢያ የተመለከተ ነበር፡፡

95ኛ ዓመታቸውን በቅርቡ ያከበሩት ሌተናንት ጄነራል ጃገማ ኬሎ ከፋሽስት ኢጣልያ ጋር ለመዋጋት የኢትዮጵያን ሠራዊት ሲቀላቀሉ 18 ዓመት እንኳን አልሞላቸውም ነበር፡፡ እኚህ ጀግና አርበኛ የካቲት 6 ቀን 2008 ዓ.ም. በዋቢ ሸበሌ ልደታቸው ሲከበር “ዕድሜ ሰጥቶኝ ከእናንተ ጋር በዓሉን ለማክበር ስለበቃሁ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፡፡ ከዚህ ሁሉ አደጋ ተርፌ የዕድሜ ባለፀጋ በመሆኔም ደስተኛ ነኝ፡፡ ለወደፊትም ፈጣሪ እስኪጠራኝ ድረስ በሰላምና በጤና እንዲያኖረኝ እለምናለሁ እናንተም ጸልዩልኝ፤” ነበር ያሉት፡፡

አዲስ አበባ ከተቆረቆረች 129 ዓመታት ቢቆጠሩም የከተማዋ ቱሪዝም የሚጠበቀውን ያህል እንዳላደገ ይነገራል፡፡ የዘርፉ ባለሙያዎችና ሌሎችም አስተያየት ሰጪዎች ለዚህ የሚያስቀምጧቸው ምክንያቶች ብዙ ናቸው፡፡ ከእነዚህ መካከል ባልተገባ መንገድ የሚንቀሳቀሱ አስጐብኚዎች ተጽዕኖ አንዱ ነው፡፡ የቱሪስት መዳረሻ በሆኑ አካባቢዎች ልመና መስፋፋቱና አልፎ አልፎ የፀጥታ ችግር መከሰቱም ይጠቀሳል፡፡

‹‹ለሕዝባችን በበለጠ ትምህርትና ዕውቀት ለማካፈል የሚችልበትን ዘዴ በመሻት ለምናደርገው ጥረት ቴሌቪዥን ተጨማሪ መሣሪያ ስለሚሆን የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን መርቀን ስንከፍት ደስ ይለናል፤ ትምህርት ለወጣቶችና ለሕፃናት ብቻ ሳይሆን ለሸመገሉም ነው፡፡ የቴሌቪዥን ጣቢያ አገልግሎቱ 

በሰው ዘር መገኛነት የምትታወቀው ኢትዮጵያ በተለይ በአክሱም ሐውልትና በላልይበላ ውቅር አብያተ ክርስትያናት በሌላው ዓለም እንድትታወቅ ሆናለች፡፡ 1700 ዓመታትን ያስቆጠረው የአክሱም ሐውልት 24 ሜትር ርዝማኔ አለው፡፡ 160 ቶን የሚመዝን ሲሆን ወጥ የሆነ ገጽታው ከአንድ 

Pages