እነሆ መንገድ ከመገናኛ ወደ ቦሌ። ጎዳናው በአዳዲስ ነገሮች ያበደ ይመስላል። አዲስ እንደ መፀየፍ፣ አዲስ ሰምቶ እንዳልሰማ ማለፍ፣ አዲስ እንደ ደንታ ቢስ

እነሆ መንገድ። ከሜክሲኮ ወደ ሳር ቤት ልንጓዝ ነው። ስትበር ያገኘናት በራሪ ታክሲ ለቃቅማ ሞልታን ቦታ ቦታ ይዘናል። ሳንዘራ በምንለቀምበት በዚህ መንገድ

እነሆ መንገድ! ከአያት ወደ መገናኛ ልንጓዝ ነው። የሄድንበትን ደግመን ልንሄድበት  የተጓዝንበትን ደግመን ልንጓዘው አቀበቱንም ቁልቁለቱንም ተያይዘነዋል። ይህም ለዛሬ ድልና ሽንፈት ሆኖ ይቆጠራል። ታሪክ ጸሐፊ ያለፈውንና የሚመጣውን አቀናጅቶ በሚያሰናኝበት የብራና ቅኝቱ የሚከተብና የማይከተብ ሀቅ እዚህ ጎዳና ላይ ይቀመራል። የታክሲያችን ወያላ የሚጠግብ አይመስልም።  “እህ ትሄጃለሽ እሙዬ? እ? አጎቴ? አክስቴ? አባቴ? እናቴ?” እያለ ያልተዛመደውን እያዛመደ አፉ ሰው ያጠምዳል። “ኧረ እንሂድ? ከቤት እስኪወጡ ልትጠብቃቸው ነው? ሞልቷል እኮ፤” ይሉታል መጨረሻ ወንበር የተቀመጡ።

​እነሆ መንገድ። ከስታዲየም ወደ ቃሊቲ ልንጓዝ ነው። ”ይገርማል ቀኑ እንዴት ይሄዳል?” ይላል ጋቢና የተሰየመ ባለባርኔጣ።

​እነሆ መንገድ። ጊዜና ሥፍራ ተጋግዘው በውስነንት ይዘውናል። መፍጠን ያቃተው ‘የጊዜ እንጂ የሰው ጀግና የለውም’ እያለ እጁን ሰጥቶና አንገቱን ደፍቶ ይኖራል። 

Pages