‹‹ለአራት ተከታታይ ቀናት ይሰጣል ተብሎ የነበረው የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና፣ ፈተናው እስከቀረበበት የመጀመሪያ ቀን ድረስ በተደረገ ክትትል ፈተናው ስለመሰረቁ የተገኘ ማረጋገጫ አልነበረም፡፡››

‹‹ለአራት ተከታታይ ቀናት ይሰጣል ተብሎ የነበረው የከፍተኛ ትምህርት  መግቢያ ፈተና፣ ፈተናው እስከቀረበበት የመጀመሪያ ቀን ድረስ በተደረገ ክትትል ፈተናው ስለመሰረቁ የተገኘ ማረጋገጫ አልነበረም፡፡››

የትምህርት ሚኒስትር ሽፈራው ሽጉጤ፣ በመላው አገሪቱ ለከፍተኛ ትምህርት መግቢያ በ800 ጣቢያዎች ለ254 ሺሕ ተማሪዎች መሰጠት ተጀምሮ የነበረው ፈተና፣ በመጀመሪያው ዕለት ግንቦት 22 ቀን 2008 ዓ.ም. እንዲቋረጥ መደረጉን ባስታወቁበት ጊዜ የተናገሩት፡፡ ተቋርጦ የነበረው ይኸው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከአንድ ወር በኋላ፣ ከሰኔ 27 ጀምሮ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2008 ዓ.ም. ድረስ  እንደሚሰጥ ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

 

* * *

‹‹እዚህ አዲስ አበባ ውስጥም በርካታ ደላሎች በትምህርት ተቋማት ዙሪያ ተሰማርተዋል፡፡ ሁሉንም የትምህርት ዓይነት በአንድ ሺሕ ብር፣ ለአንድ የትምህርት ዓይነት 200 ብር ከከፈላችሁ ፈተናውን እኛ እንሰጣችኋለን ብለው እየተንቀሳቀሱ ነው፡፡››

የትምህርት ሚኒስትር ሽፈራው ሽጉጤ፣ የሚኒስቴሩን የስምንት ወራት የሥራ አፈጻጸም፣ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሚያዝያ 6 ቀን 2008 ዓ.ም. ባቀረቡበት ወቅት የተናገሩት፡፡ በትምህርት ዘርፍ ካለው የደመወዝና የጥቅማ ጥቅም ችግር ባለፈ ኩረጃ፣ የፈተና ስርቆትና የትምህርት ማስረጃ ሽያጭ ማቆጥቆጡንም  ለፓርላማው የዚያኑ ዕለት መናገራቸው ይታወሳል፡፡