የባህር አይጥ

መጠሪያ ስሙ የባህር አይጥ ይሁን እንጂ አይጥ አይደለም፡፡ የትላትል ዝርያ ቢሆንም በቅርፁ ለየት ይላል፡፡ ሰውነቱ በአጭርና የመቆንጠጥ ባህሪ ባለው በፀጉር የተሸፈነ ሲሆን የሚራመደውም ፀጉሩን በመጠቀም ነው፡፡

ኪድስ ባዮሎጂ በድረ ገጹ እንዳሰፈረው፣ በሰሜን አትላንቲክና በሰሜን ባህር፣ በገልቲክ ባህርና በሜዲትራኒያን በብዛት ይገኛል፡፡ ከራሱ ቁመት የሚበልጡትን ጨምሮ ይመገባል፡፡ ቀን ላይ ራሱን በአሸዋ ውስጥ ቀብሮ የሚውል ሲሆን፣ ለምግብ የሚመጣው ማታ ላይ ነው፡፡

የባህር አይጦች ከ7.5 እስከ 15 ሴንቲ ሜትር የሚረዝሙ ቢሆንም እስከ 30 ሴንቲ ሜትር የሚረዝሙ፣ እንዲሁም እስከ 30 ሴንቲ ሜትር የሚያድጉም አሉባቸው፡፡