አናኮንዳ

አናኮንዳ በዓለም በክብደታቸው ትልቅነት ከሚታወቁት የእባብ ዓይነቶች ቀዳሚው ነው፡፡ ሲወለድ ቁመቱ አንድ ሜትር ሲሆን፣ ሲያድግ እስከ 8.6 ሜትር ድረስ ይረዝማል፡፡ የጐልማሳ አናኮንዳ እስከ 204 ኪሎ ግራም የሚመዝን ሲሆን፣ የሚመገበው ደግሞ ኤሊን ጨምሮ እንስሳትን ነው፡፡

አናኮንዳ ውኃ ውስጥ በማድፈጥ ውኃ ለመጠጣት የሚመጡ እንስሳትን በመብላት ይታወቃል፡፡ በመዝለል የሚታወቅ ቢሆንም፣ ብዙ ጊዜውን የሚያሳልፈው መሬት ላይ በመተኛት ነው፡፡

በደቡብ አሜሪካ የሚገኘው አናኮንዳ፣ እንደ ሌሎች የእባብ ዝርያዎች መርዛም አይደለም፡፡ አዞዎችንም ይሁን ሌሎች እንስሳትን የሚገድለው ላያቸው ላይ ተጠምጥሞ በመሰባበር ነው፡፡ አጋዘንና ነብር እንዲሁም መለስተኛ የዓሳ ዝርያዎችን አፉን ከፍቶ መዋጥ ይችላል፡፡ ናሽናል ጂኦግራፊ እንዳሰፈረው፣ የአናኮንዳ የመኖር ዕድሜ አሥር ዓመት ነው፡፡