Latest upload

ቅፅ 29 ቁጥር 2581/ ረቡዕ - ጥር 14 - ቀን - 2017
በትግራይ ክልል ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ከሂጃብ መከልከል ጋር በተያያዘ የተቃውሞ ሠልፍ አደረጉ - ስለጉዳዩ የተጠየቀው የትምህርት ሚኒስቴር ተቋማዊ ክብሩን ያልጠበቀ ምላሽ ሰጥቷል - ‹‹ብንዘገይም አሁንም አልረፈደምና በአፋጣኝ እንዲፈታ እንሠራለን›› አቶ ጌታቸው ረዳ፣ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት በትግራይ ክልል አክሱም ከተማ በሚገኙ አምስት ትምህርት ቤቶች የሚማሩ 159 ሙስሊም ሴት ተማሪዎች፣ በሂጃብ ምክንያት ከአንድ ወር በላይ ከተገለሉበት ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ፣ በክልሉ ትምህርት ቢሮና ፍርድ ቤት የተሰጠው ትዕዛዝ እንዲከበር የሚጠይቅ የተቃውሞ ሠልፍ ትናንት ጥር 13 ቀን 2017 ዓ.ም በመቀሌ ከተማ ተደረገ።

ቅፅ 29 ቁጥር 2580/ እሑድ - ጥር 11- ቀን - 2017
የኢትዮጵያ ጂዲፒ በውጭ ምንዛሪ ለውጡ ምክንያት ወደ 100 ቢሊዮን ዶላር መውረዱ ተገለጸ - የአገሪቱ የውጭ ዕዳ ጂዲፒ ጥምርታ ለደሃ አገሮች ከተቀመጠው ጣሪያ አልፏል የኢትዮጵያ ኖሚናል ጂዲፒ (የዋጋ ንረትን ታሳቢ ያላደረገ አጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት) በዶላር ሲተመን፣ በሰኔ ወር 2016 ዓ.ም. ከነበረበት 207 ቢሊዮን ዶላር በሦስት ወራት ውስጥ ወደ 100 ቢሊዮን ዶላር መውረዱ ተገለጸ፡፡

ቅፅ 29 ቁጥር 2579/ ረቡዕ - ጥር 7 - ቀን - 2017
የትግራይ ክልል ተፈናቃዮች የኢትዮጵያ ሕዝብ ወደ ቀዬአችን እንድንመለስ ድምፅ ይሁነን ሲሉ ጠየቁ ከሰኞ ጥር 5 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ለሦስት ቀናት የተቃውሞ ሠልፍ በመቀሌ ከተማ እያካሄዱ ያሉት የትግራይ ክልል ተፈናቃዮች፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ ድምፅ እንዲሆናቸው ጠየቁ፡፡ በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መሠረት ወደ ተፈናቀሉበት የመኖሪያ ቀዬ ለመመለስ የሚመለከታቸውን የስምምነት ተፈራራሚ አካላትን ሲጠይቁ ቢቆዩም፣ እስካሁን ምላሽ የሚሰጣቸው ማጣታቸውን ተናግረዋል፡፡